የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከሶስት የንግድ ባንኮች እና አንድ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ጋር የብር 152 ሚሊዮን የብድር ውል ስምምነት መጋቢት 03 ቀን 2010 ዓ.ም በዋናው መ/ቤት ተፈራርሟል፡፡
የብድር ስምምነቱ የተካሄደው ከእናት ባንክ፣ ሕብረት ባንክ እና ብርሃን ባንክ ሲሆን ከማክሮ ፋይናንስ ተቋማት መካከል ደግሞ ከአዲስ ብድርና ቁጠባ አ.ማ. ጋር ነው፡፡
የብድር ስምምነቱ የተፈረመው በኢትዮጵያ ልማት ባንክ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ፋይናንሲንግ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ተሾመ አለማየሁ እና ከአራቱ የፋይናንስ ተቋማት ፕሬዝዳንቶች ጋር ነው፡፡ ይህ የብድር ውል ስምምነት በቀጣይም ከሌሎች የፋይናንስ ተቋማት ጋር የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የብድር ስምምነቱ ዓላማ የፋይናንስ ተቋማቱ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሥራ ማስኬጃ ብድር እንዲሰጡ መሆኑን አቶ ተሾመ ተናግረዋል፡፡
የብድሩ ምንጭ ዓለም ባንክና የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንኮች ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ ካበደሩት 276 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ውስጥ መሆኑ ታውቋል፡፡
ተጨማሪ መረጃ የሚያስፈልግ ከሆነ የኢትዮጵያ ልማት ባንክን ድህረ ገፁን ይመልከቱ:
www.dbe.com.et/homenew/index.php/9-main-menu/home/131-2018-03-13-22-50-38